Skip to main content

Recent News

Body:

የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሁለተኛ ዙር በዘመቻ ለአንድ ወር የሚቆይ ከዞን እስከ ወራዳና ቀበሌ ድረስ የድጋፍ ክትትል ስምሪት ዙሪያ ለአመራሮችና ለሠራተኞች የኦሬንቴሺን መድረክ አካሄደ ።

በመድረኩ ላይ የቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በመጀመሪያ ዙር በዘመቻ ሥራ በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ለማምጣት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል ።

በተጨማሪም በሁሉም ዙር የሁሉም ዘርፍ የቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በማቀናጀት እስከ ቀበሌ ድረስ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የካቲት 17/2017 ጀምሮ ለተከታታይ 30ቀናት የሚቆይ ስምሪት የጋራ ስምምነት በመፍጠር አሰማርተዋል ።

በዘመቻው በትኩረት ከሚሰሩ ጉዳዮች መካከል አጫጭር ገበያ ተኮር ስልጠና ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዙሪያ፣ የአንድ ማዕከል ግንባታ ጉዳይ፣ ኢንተርፕራይዞችን በባዮሜትሪክስ መዝግቦ የመያዝ ስራ ፣ ኮሌጆች ቴክኖሎጂዎችን ከማምረት አንፃ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት፣ የባዛር ዝግጅት ፣ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ሥለጠና ዙሪያ፣ ብሔራዊ መታወቂያና በመደበኛ ሥራዎችን እንደሚያካትት ተገልጿል ።

Body:

የሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ ወጣቶች መንግስት ያመቻቸውን እድል ተጠቅመው በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ሀብት ማፍራት የቻሉትን የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት ማድረጋቸውን ቢሮ ገለፀ

በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ጨምሮ የቢሮ ምክትል ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት በመገኘት ወጣቶች ተደራጅተው በመስራት የራሳቸውን ሀብት ከማፍራት ባሻገር ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን ማየት ተችሏል ።

Body:

የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ 2ኛ ዙር በዘመቻ ድጋፍና ክትትል ከዞን ፣ ወረዳና እስከ ቀበሌ ድረስ ለ30 ተከታታይ ቀናት የሚቆየውን ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አመራርና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደዋል ።

በዘመቻው በትኩረት ከሚሰሩ ጉዳዮች መካከል አጫጭር ገበያ ተኮር ስልጠና ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዙሪያ፣ የአንድ ማዕከል ግንባታ ጉዳይ፣ ኢንተርፕራይዞችን በባዮሜትሪክስ የመመዝገብ ስራ፣ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ሥለጠና ዙሪያ፣ ብሔራዊ መታወቂያና በመደበኛ ሥራዎችን መሆኑን ተገልጿል ።

በመድረኩ ላይ የቢሮ ምክትል ሀላፊና የስልጠናና ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፍሰሀ ፍቾላ ፣ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በርሁን ባራሳ ጨምሮ የቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች እንድሁም የዞን አመራሮች በመገኘት የጋራ መግባባት በመፍጠር ወደ ዘመቻው መሰማራታቸውን ተገልጸዋል ።

Body:

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የከተማና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ 2017 የበጀት አመት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ገመገሙ::

የእቅድ አፈጻጸም መድረኩን የመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/መስቀል የ2017 በጀት አመት የቢሮው የ6 ወር የአፈፃፀም በዝርዝር ገምግሟል ።

የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀገሬጽዮን አበበ የ2017 የበጀት አመት የቢሮው 6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን በዝርዝር ያቀረቡት ስሆን ሁሉም ተግባር በእቅዱ መሰረት የተከናወኑ መሆናቸውንና የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን አንስተዋል ።

ቢሮው ሰው ተኮር ስራ እየሰራ ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተለይም የድጋፍና ክትትል ስራዎች ለሌሎች ቢሮዎች ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን አንስተው፣ በጥንካሬ ያየናቸው ስራዎች ተጠናክሮ እንድትቀጥሉ ፣ በቀጣይነት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በታቀደው እቅድ መሰረት የተሻለ ውጤት እንድመጣ አጠናክሮ መስራት ያሰፈልጋል ተብሎዋል ።

Body:

ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ገለፀ ።

ቢሮው ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ማልጋ ወረዳ በመንግሥት ድጋፍ በተለያዩ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት በማድረግ ከወረዳ አመራሮች ጋር የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል ።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድሚያ በመስጠት በተሠራው የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ።

ወጣቶች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የተፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ክህሎትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በመስጠት ወጣቶች በተሰማሩበት ስራ መስክ ይበልጥ ውጤታማ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል ።

ዛሬ ጉብኝት የተደረገው ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ማልጋ ወረዳ በመንግስት የእርሻ መሬት በተጨማሪ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ገብስና ስንዴ ውጤት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል ።

በቢሮ ምክትል ሀላፊና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ ወጣቶች በተለያዩ ሥራ ዘርፎች ከማሰማራቱ አንፃር tvet ኮሌጆች ሠልጣኞች ከማስመዝገብ አንፃር ነባር ኢንተርፕራይዞች ድጋፍና ለውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር የአንድ ማዕከል ግንባታ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች መስተካከል እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

ማልጋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ኩኪሳ በበኩላቸው ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያሉ አጋጣሚዎችን በመጠቀም እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በሥራ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰሩ ተናግሯል ።

Body:

የሲዳማ ክልል የፖለቲካ አመራሮች በሥራ እድል ፈጠራ ስራ ላይ የሰጠው ትኩረት ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ገለፁ

በክልሉ በሁሉም ዞኖች የገጠር ሥራ እድል ፈጠራ ሥራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራው የድጋፍና ክትትል ቡድን ለአራት ተከታታይ ቀናት እያደረጉ የቆዩትን ድጋፍና ክትትል ጨረሰው ግብር መልስ በሰጡበት ገልጸዋል ።

ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች ከሪፖርት ባሻገር ያሉበትን የአፈፃፀም ሁኔታ በመመልከት ችግሮችን ለመፍታትና አፈፃፀሙን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ዶ/ር ተሻለ አንስተዋል ።

ቡድኑ ከቢሮ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የተመረጡ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን እና የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን በመመልከት በዘርፉ አበረታች ውጤት መገኘቱንና ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆኑ በርካታ ስራዎችን ማየት መቻላቸውን ገልጸዋል።

Body:

Dijitaale Gashshooti 2030 Aana Qoqqowu Massagaanora Huwanyoote Kalaqate Bare Harinsi.

Sidaamu Qoqqowi Loosu Dandootenna Interpiraayzootu Latishshi Biiro Sayinsenna Tekinoloojete Ejense Innoveeshiinetenna Tekinoloojete Ministere Ledo Halamatenni Dijitaale Gashshoote ( Digital Government 2030) straateejje Aana Qoqqowu Massagaanora Huwanyoote Kalaqate Bare Harissino.

Barete aana Sidaamu qoqqowi loosu dandootenna interprayzootu latishshi biiro layinki sooreessinna qoqqowu ogimmate dandoo buuxo ejensehu qaru dayrektere kalaa Tewodros Gawiiwihu, 2030 dijitaale miinja hasi'noonni deerra iillishate mixo aana massagaano huwachishate hende qixxeessinoonni bare ikkase xawisino.

Kalaa Tewodros sufeno, uurrinshuwa ayeetano uyitanno owaante dijitaale assa lifixanna owaatamaano kassi assitino hattono yannate ledo hadhannota assate lowo injo kalaqantannota huwachishino.

Qoqqowu sayinsetenna tekinoloojete ejensehu qaru dayrektere kalaa Tafarri Baraasihu, gobbate lopho ollohisate tekinoloojete safote latishshi hala'lanna buuxama qara ikkase kule, duuchanta loossa dijitaale assate mootimma illachishshe loossanni no yiino.

Dijitaali gashshoote 2030 straateejje aana massagaanote qixxeessinoonni huwanyootu bare gibrinna, manufakcheringe, shiilote, tuurizimenna addi addi latishshu loossa dijitalayize asse horonsira guma abbatenna uyinanni owaante yannitte assate mootimma amaddino mixo loosu aana hosiisate ikkinota xawisino.

Dijitaale gashshoote 2030 ltophiyu gobbate giddo egenno horonsiratenni dijitaale miinja buuxisiisate baalanta loossa tenne hanqafonni sufantanno gede illachinshoonnita xawisino.

የዲጂታል መንግስት 2030 ስትራቴጂ ላይ ለክልሉ አመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ ።

የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ዲጂታል መንግስት 2030 ስትራቴጂ ላይ ለክልሉ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂደዋል ።

በመድረኩ ላይ ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይረክተር አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ 2030 ዲጂታል ኢኮኖሚ ዕውን ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ ላይ ለክልሉ አመራሮች የተዘጋጀ የግንዛቤ መድረክ መሆኑን ተናግሯል ።

አቶ ቴዎድሮስ አክለው ተቋማት የሚሰጡትን ሁሉንም አገልግሎት ዲጂታል ማድረግ ቀልጣፋና ተገልጋዮችን የሚያረካ አገልግሎት ለመስጠት የታለመ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ከጊዜና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር መሄድ ያስፈልጋል ብሏል።

የሲዳማ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይረክተር አቶ ቴፈራ ባራሳ በበኩላቸው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማፋጠን የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ሁሉንም ሥራ መንግስት ዲጂታላይዝ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

የስልጠና መድረኩ የዲጂታል መንግስት 2030 ስትራቴጂ ዙሪያ ለክልሉ አመራሮች ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ሆኖ ግብርናን፤ ማኑፋክቸሪንግ፤ ማዕድን ፤ ቱሪዝምንና ሌሎች ልማት ስራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግና የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንድሁም የሚሰጠው አገልግሎት ዘመናዊ ለማድረግ በሀገር ደረጃ የተጀመረ ስራ መሆኑን አቶ ቴፈራ ተናግሯል ።

ዲጂታል መንግስት 2030 ስትራቴጂ ኢትዮጵያ የሀገር በቀል ዕውቀትን በመጠቀም ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ ሁሉንም ተግባራት በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጿል ።

Body:

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን ወደ ሲዳማ ክልል ገቡ ።

ሀዋሳ: ህዳር 22/2017ዓ.ም የቢሮው ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን ከቢሮው የማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ድጋፍና ክትትል የሚያደርገው ቡድን በሲዳማ ክልል በአራት (4) ወራት ውስጥ በክልሉ የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ቡድኑ በመስክ ምልከታው ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ አሠሪና ሠራተኛ ግንኙት እና ከተቋማት ግንባታ አኳያ የተሰሩ ሥራዎችን እስከታችኛው የዘርፉ መዋቅር ድረስ በመውረድ የግል ኮሌጆችንና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራንና ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውሮ እንደሚመለከት ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ገልጸዋል ።

አክለውም የድጋፍና ክትትሉ ዓላማ የሪፎርም ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ፤ ባሳለፍነው አመት ያየናቸው መልካም ስራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ከማድረግ አኳያ ያለበትን ደረጃ ለማየት መሆኑን አንስተው ፤ በአፈፃፀም ሂደት ለገጠሙ ችግሮች የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ በዘርፉ የታቀደውን ዕቅድ ማሳካትና የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲሆን ቡድኑ ድጋፍና ክትትሉን እንደጨረሰ በተገኘው ግብዓት መነሻነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ይሆናል ብለዋል።

በመቀጠልም የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀገረጽን አበበ በበኩላቸው ቡድኑን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሥራውን ለማሳለጥ በየጊዜው እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትል ትልቅ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አንስተው የ2017 በጀት አመት የአራት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል ።

እንደ ሃላፊዋ ገለፃ ቢሮው በአራት ወራት ውስጥ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

Body:

ፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን የዳዬ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ጉብኝት በተጨማሪ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ እና ቦና ዙሪያ ወረዳ ተደራጅተው በተለያዩ ሥራ ላይ ተሰማርተው ያሉ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አድርጉ ።

ህዳር 23/2017ዓ.ም ቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ እና ቦና ዙሪያ ወረዳ ተደራጅተው በተለያዩ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት አድርጓል ።

የድጋፍና ክትትል ቡድን የዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት በተጨማሪ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡ ወጣቶችን ተዘዋውረው በመመልከት በክህሎት፤ በከተማ እና በገጠር የሥራ እድል ፈጠራ በተሰራው ስራ የመጣው ውጤት አበረታች መሆኑን ተናግሯል ።

ቡድኑ ወጣቶች በዞኑ ውሰጥ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ እንድሁም በተለያዩ ሥራ ላይ የተሰማሩትን ተመልክተዋል ።

ቡድኑ ባዩት ሥራዎች ደስተኞች መሆናቸውን ያነሱት ስሆን በ ዘርፋ አበረታች ውጤት እንድገኝ እና የሪፎርም ስራዎች መሬት በማስረገጥ፤ ቢሮው በበሳል አመራር ሰጭነትና በተቋም ግንባታ ተምሳሌት እንድሆን ላደረገችው የቢሮ ሃላፊዋ ክብርት ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ እና ለማኔጅመንቱ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል ።

የመስክ ምልከታውና ጉብኝቱ በነገው ዕለትም በተላያዩ ወረዳዎች ላይ የሚቀጥል እንደሆነ ተጠቁሟል ።

Body:

Sidaamu Qoqqowi Loosi Dandootenna Interpieaayizootu Latishshi Biiro ATI (ADEY) Yaamantanno Mootimma ikkitinokki Uurrinsha Ledo Halamatenni Gibirinnu Handaarinni Tantanante Loosu Giddora Eino Wedella Sasu Mereershira Mind Set, Business Planetenna Entrepreneur Ship Qajeelsha Uyiinanni Afammannita Xawinsi.

Qajeelshu Bare Aana Leelle Hanafisiisinohu Qoqqowu Loosu Dandootenna Interpiraayizootu Latishshi Biiro Aantichunna Loosu Kaayyo Kalaqo Handaari Sooreessi Kalaa Kefiyalewu Kebedehu, Hiitee injoono Wedellu Loosu Kaayyo Kalaqo Yine Amandoonni insheetiiwe Qoqqowu Giddo Noo Elto Bande Wedellinke Horaameeyye Assate Jawa irko ikkitinota Kule, Biiro Tenne Hajo Baxxino illacha Tugge Loossanni Noota Xawisino.

ATI (ADEY) Yaamantanno Mootimma ikkitinokki Uurrinsha Qoqqowu Giddo 6 Woraddara Wedellaho Qajeelshanna Babbaxxitino irko Assitannota Qummi Asse, Techo Barra Umikki Doogichora Sase Woradda Daalle Woradira, Shabbadiini Woradiranna Lokka Abbaayyu Woradira Xaphoomunni 340 Wedellira Qajeelsha Uuyinanni Afantannoha ikkanna Laayikki Dooyichono Gattino Woraddara Aante Suffannota ikkase Huwachishino.

Qajeelshuno 5 Aantanno Barrubbara Sufannoha ikkasi Kulloonni.

ሲዳማ ክልል ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ከ ATI ( ADEY ) የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆኑ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በግብርና ዘርፍ በ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶችን በሦስት ማዕከላት ላይ በቢዝነስ ፣ የክህሎት እና ኢንተርፕርነር ሽፕ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ተገለፀ

በስልጠናው ላይ ተገኝተው ያስጀመሩት ሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የሥራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ በበኩላቸው ፣ ክልላችን ሁሉም አማራጮች ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ኢኒሼቲቭ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ሀብቶቻችን ለይተን ወጣቶቻችንን ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰራው ስራ ትልቅ ውጤት ማስገኘት መቻሉን ጠቅሰው ፣ ቢሮውም የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥተው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

ሀላፊው አክለውም ATI (ADEY) የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆኑ ድረጅት በክልላችን ውስጥ ለ6 ወረዳዎች ላይ ወጣቶችን ለማሰልጠን እና የተለያዩ ድጋፍ በማድረግ ከቢሮው ጋር ተቀናጅተው እንደምሰራና ዛሬ ለሦስት ማዕከላት ዳሌ ወረዳ ፣ ሸባድኖ ወረዳ እና ሎካ አባያ ወረዳ የመጀመሪያ ዙር 340 ወጣቶችን እያሰለጠኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ስልጠናውም ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑንና ለሌሎች ወረዳዎች ላይም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሲዳማ ክልል ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የህዝብ ግኙነት ዳይሬክቶረት

ግንቦት 11/2016ዓ.ም

ሀዋሳ

Body:

Sidaamu Qoqqowi Loosu Dandootenna lnterprayzootu Latishshi Biiro Massagaano Hawaasi Tegbaareedi Pooli Tekinikete Kolleejje Addi Addi Loosu Towaanyo Assitu.

Towaanyote Aana Biirote Sooreette Dukko Hageretsiyoon Abbebeti Lendanna Wo'manti Manajimentete Miilla Afantinoha ikkanna Kolleeje islancho Qajeelsha Aate Widoonni Noo Loossa, Qooxeessu Qarra Tirtanno Tekinoloojja Burqisate Widoonni, Kolleeje Giddo Eo Burqisate Widoonni Loonsanni Hee'noonnire Hattono Addi Addi Giddooyidi Loossa Towaanyo Assinoonni.

Towaanyotennino, Kolleejje Qansoota Addi Addi Ogimmanni Qajeelsite lkkado Dandoo Afidhanno Qansoora Qajeelshate Ledo Dagate Mitiimmuwa Tirtanno Tekinoloojjanna Kalaqu Loossa Loossanni Afantannota Towaanyotenni Buuxa Dandiinoonni.

Kolleeje Tayixe Diro Tekinoloojetenna Dandoote Heewora lkkitanno Addi Addi Tekinoloojjanna Kalaqu Loossa Burqisatenni, Beeqqateno lkkado Qixxaawo Assitanni Aana heeransanna Giddo eo Burqisate Jawata Loossa Loossanni Afantannota Xawinsoonni.

ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አመራሮች የሀዋሳ ተግረ_ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

በጉብኝቱ ላይ ሲዳማ ክልል ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት የቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ ጨምሮ የቢሮ የማኔጅመንት አባላት የተገኙ ስሆን ኮሌጁ ጥራት ያለውን ስልጠና ለመሰጠት ያለውን ዝግጅት፣ የአከባቢውን ችግር የሚፈታ ቴክኖሎጂ ከማመንጨት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን፣ የውስጥ ገቢ ለማፍራት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተጎብኝቷል።

በጉብኝታቸው ኮሌጁ ዜጎችን በተለያዬ ሙያ በማሠልጠን በክህሎት የበቁ ዜጎችን ከማፍራት ባለፈ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ የሆኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማፍራት የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው መሆኑን ተመልክቷል።

ኮሌጁም ዘንድሮ በክልል ደረጃ የሚደረገውን የቴክኖሎጂና ክህሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማዘጋጀት በቂ ዝግጅት ማድረጉን በጉብኝቱ ማየት መቻላቸውንና የውስጥ ገቢ ለማሳደግ አመርቂ ስራዎችን መሰራታቸውን ተገልጸዋል ።

ቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት

ሰኔ 07/2016 ዓ. ም

ሀዋሳ

Body:

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አዘጋጅነት በለኩ ከተማ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር የታለመ ኤግዚቢሽን በይፋ ተጀምረ።

በለኩ ከተማ በይፋ በተከፈተው የኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን ላይ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደረሰ ፣ የለኩ ከተማ ከንቲባ አቶ ፀጋዬ አባተ ፣ የለኩ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታደለ እንዲሁም የዞን እና የከተማው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተገኘዉ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደረሰ "ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ በዛሬው እለት በለኩ ከተማ በይፋ ያስጀመርነዉ የኤግዚቢሽን መድረክ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።" ብሏል።

አክሎም በፍጥነት እያደገ ባለው የሀገራችን ኢኮኖሚ የሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ትኩረት ተሰቶበት እየተሰራበት ይገኛል ያለ ሲሆን ብዙ ሥራዎች የሚፈጠሩትም ኢንተርፕራይዞችን በመመስረት እና በማበረታታት መሆኑን በመግለፅ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የማህበራዊ ኢኮኖሚ መሠረት በመሆናቸው የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች እንዲቋቋሙ የገበያ ትስስር መፍጠር ተገቢ መሆኑን ገልጿል።

በመጨረሻም እንደ ክልላችንም ሆነ በዞናችን ደረጃ የኢንተርፕራይዞች በገበያ ትስስር እጥረት ምርታቸው እንዳይሸጥ ስለሚያደርግ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ስለ ኢንዱስትሪው እንዲያውቁ እና ልምድ እንዲለዋወጡ በዛሬው እለት በለኩ ከተማ አጠቃላይ በዞኑ ስር የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በተገኙበት የኤግዚቢሽን መድረክ በይፋ ከፍተን አስጀምረናል ብሏል።

የለኩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፀጋዬ አባተ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉን ካስተላለፉ በኋላ የኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን በከተማችን በመዘጋጀቱ ደስታችን ከፍ ያለ ነዉ ያሉ ሲሆን የከተማዋ ማህበረሰብ ኢንተርፕራይዞቹ አምርተዉ ያቀረቧቸዉን ምርቶች በመሸመት እንዲያበረቷቷቸዉም ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል።

በዛሬዉ እለት በይፋ የጀመረዉ የኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን ከሰኔ 5-8 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

ምንጭ:_ የሲ/ብ/ክ/መ/የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት

ሰኔ 6/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ

Body:

Sidaamu Dagoomu Qoqqowi mootimma loosu Dandootenna Interpayiizottu Latishshi Biiro Sayinsenna Tekinoloojete Ejjense Sayinsenna Tekinoloojete gumma garunni horoonsiratenni lophonna latishsha ollohisiissa hasiissannota xawinsi.

Tenne xawinsoonnihu Sidaamu Qoqqowi loosu dandootenna Interprayiizottu latishshi biiro Dijitaale istirateeje aana assinoonni hasaawinna Sayinsenna Tekinoloojete Ejensenni lattino sistemubba faajjenni maassiinsi yannaraati.

Barru hasaawa hanafisiisinohunna lattino sistemubba maassire faninohu Sidaamu Qoqqowi Jireenyu Paarte Borro Mini Sooreessi Kalaa Abirihaam Marshaallohu, yannate ledo qaafatenni qoqqowu giddo amandoonni latishshu mixo woyyaawino garinni jeefisate tekinoloojete ledo fiixoomanna horoonsira hasiissannota huwachishino.

Tekinolooje Mootimmate uyinanni owaante lifixisatenni sa'e woxe, wolqanna yanna ajishatenni manchi beetti heeshsho shotisatenna woyyeessate jawu qeechi nooseta xawissinoti Qoqqowu Loosu, Dandootenna Interpirayzootu Latishshi Biiro Sooreette Dukko Hageretsiyon Abbebeti, Tekinolooje horoonsira gade assira hasiissannota coydhino.

Handaaraho sa'e sa'e wo'munni wo'ma Tekinolooje horoonsirate widoonni laooshshu, huwanyootunna dandoote qarri leellannota xawissino sooreette aantino yannara konne xaawatenni handaaraho hasi'noonni guma abbate loonsannita buuxissino.

Tekinoloojetenni irkisamatenni mootimmate uyinanni owaante woraqatunni co'ittenna lifixa assate loonsanni hee'noonnita xawisinohu kayiinni Qoqqowu Sayinsenna Tekinoloojete Ejense Qaru Dayrekiterichi Kalaa Tefarri Baraasiho. Qoqqowo Dijitaale Miinjinni xaadisate Ejense loossanni nootano hattonni.

Barraho Ejensete lattino Weebisaytenna Portaale maassante owaantette fano ikkitino.

Body:

Federaalete Loosunna Dandoote Ministere Qixxeessonni 3kki Doyicho Gobboomu Dandoote Heewo "Dandoo Heewisamaanchimmate" Yaanno Massagote Qaalinni"Addisawawu Quchumira Techo Hanaffino.

Heewote Amanyoote xaphoomu Ministerchi D/r Abiy Ahimedihu Hanafisiisino.

Sidaamu Qoqqowi Deerrinni Heewisante Albisa Ikkitino Dandootenni, Assoote Illachishshino Xiinxallonni, Tekinoloojete Heewonni Beeqqitanni Afantanno.

Sidaamu qoqqowi loosu dandootenna interprayizootu latishshi biiro 2kinna tekinikete ogimmate qajeelshunna interprayizootu irko handaari sooreessi kalaa Fiissi Fichoolihu, heewo qoqqowunna gobbate deerrinni dandootenni heewisamaancho ikkino qansicha kalaqate jawa irko nooseta xawisino.

Heewoteno dandootenni 18 qajeelsiisaano, 14 qajeelaano, assoote illachishshino xiinxallonni 1,tekinoloojetenni qajeelsiisaano 1, qajeelaano1, interprayizootunni 1 beeqqitanni noota xawinsoonni.

Sidaamu qoqqowi xaphoomunni 36 heewonni beeqqanni afamanno.

Heewono onkoleessa 14 kayisse 18 geeshsha keeshshitanno.

Body:

Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Loosu Dandootenna Interprayizootu Latishshi Biiro Mootimmate Rosunna Qajeelshu Kolleejjuwa Xaageeshsha Noota Loosu Gumulshi Keeno Assitino.

Keenote hasaawi aana leeltinoti Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma loosu dandootenna interprayizootu latishshi biiro sooreette dukko Hageretsiyooni Abbebeti rosunna qajeelshu kolleejjuwa dikkote hasantanno mereersite ogimmate handaarranni qansoota ikkadu garinni qajeelsa qara loossa ikkansa kulte, xaa geeshsha nooti kolleejjuwanniti loosu jeefo danchano ikkituro sunfe lowori loosama hasiissanno loossa noota xawissino.

Dukko Hageretsiyooni leddeno, kolleejjuwa uurrinshannihanna harancho qajeelsha aatenna qajeelaano adhate woraddatenna haja la'annonsari ledo qinaawe loosate widoonni laanfe noota kulte, tini suffe taaltanno gede qaagiissitino.

Mite mite kollejjuwa noonsa mitiimmuwanni rakke fula agartannota xawisse, kolleejjuwate gumaamimmara mootimma hasiissanno irko baala assitannota coyidhino.

Biirote layinkinna rosunna qajeelshu handaari sooreessi kalaa Tesfaye Deewisohu qajeelaano adhatenna galo qajeelaano qolate widoonni lowo xe'ne leeltannota xawise, sunfe illacha tunge loosa hasiissanno yiino.

Biirote layinkinna tekinoloojete reekkonna industurete ekstenshiine handaari sooreessi kalaa Azmeri Ammanohuno isiwidoonni, addi addi tekinoloojja reekkatenni dagate mitiimma tirate loonsanni hee'noonnita kule, tenne tekinoloojjara kaima ikkitinori qajeelshu kolleejjuwa ikkansanni dhukansa bowirsate illacha tunge loonsanni hee'noonni yiino.

Keenote bare beeqqitino kolleejjuwate massagaanono leeltinonsa laanfe tidhatenni suffe murciraanchimmatenni loossannota xawissino.