Skip to main content

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፌ ጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የሚመራው የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች የሥራና ክህሎት ቢሮ በኩል የተሰሩ ስራዎችን ጉብኝት ማድረጉን ጀመሩ ።

image news

የምክር ቤቱ አፌ ጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደና ምክትል አፌ ጉባኤ ክቡር አቶ ዘነበ ዘርፉን ጨምሮ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን እና በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ተገኝተው የሥራና ክህሎት ቢሮ በኩል የተሰሩ ስራዎችን ተዘዋውሮ እየተመለከቱ ይገኛሉ ።

ቢሮው በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ ዋራ ቀበሌ ላይ በግብርና ዘርፍ በ57 ሄክታር ላይ 300 ወጣቶችን በ57 ኢንተርፕራይዝን አደራጅተው ወደ ስራ ያስገባውን መመልከት የጀመረው ምክር ቤቱ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ ዶንጎራ ቀበሌ እንድሁም በአለታ ወንዶ ከተማ አሰተዳደር ሻዕቻ ቀበሌ ላይ መንግስት ያመቻቸውን እድል በመጠቀም የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል ።

ጉብኝቱም በለሎች አከባቢዎች ላይ የሚቀጥል መሆኑን ተገልጿል ።