Skip to main content

የኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት እና የማእከላት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት

  1.  ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸዉ ነገሮች

   ሐ) በስራ ፈላጊነት ለመመዝገብ የሚጠየቁ መስፈርቶች

  1. በሚኖርበት ከተማ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ያለው/ላት፣
  2. የከተማ ነዋሪነት መታወቂያ የሌለው/ላት ከስደት ተመላሽ ስራ ፈላጊዎች ከሆኑ የስደት ተመላሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወይም ሌሎች አግባብነት ካላቸው ተቋማት ህጋዊ ማሥረጃ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣ 
  3. የከተማ ነዋሪነት መታወቂያ የሌለው/ላት ከሆነ ቀድሞ ከሚኖርበት/ከምትኖርበት የገጠርም ሆነ የከተማ ቀበሌ አስተዳደር ማንነቱን/ቷን የሚገልጽ መሸኛ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፣ 
  4. እድሜው ከ18 እስከ 60 የሆነ/ነች፣ 
  5. የኢትዮጵያ ዜጋ የሆነ/ነች፣
  6. ለመስራት ፍላጎትና ችሎታ ያለው/ላት፣
  7. በራሱም ሆነ በቅጥር ቋሚ የገቢ ምንጭ/ቋሚ ስራ የሌለው/ላት፣

2. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አደረጃጀት አማራጮች

            2.1 በግል የሚቋቋም ኢንተርፕራይዝ መስፈርት

  1. የግል ኢንተርፕራይዝ ምስረታ የማመልከቻ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የስራ አጥ መታወቂያ ካርድ፣
  3. የአመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
  4. የነዋሪነት የመታወቂያ ካርድ፣
  5. ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው መሆን፣
  6. የአዋጭነት የንግድ ስራ እቅድ ማቅረብ፣
  7. በሚዘጋጀው የምዝገባ ቅጽ ላይ የንግድ ስራ አድራሻውን በመሙላትና በፊርማው በማረጋገጥ ማቅረብ የሚችል፣
  8. የመነሻ ካፒታል ማስረጃ፣ 
  9. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ 
  10.  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው የስራ መስኮች)
  11.  ለኢንተርፕራይዝ ምስረታ በግንባር በመቅረብ የሚፈለግበትን ፎርማልትዎችን ሟሟላት  የሚችል፤ 

 

     2.2. የኀብረት ሽርክና ማኀበር አደረጃጀትና መስፈርት

  1. በጥቃቅንና አነስተኛ ለመደራጀት ለአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የቀረበ ጥያቄ
  2. የማህበሩ አባል ለመሆን የቀረበ የግል ማመልከቻ ከሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ማቅረብ
  3. የማህበር መመስረቻ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ የሚችል
  4. የስራ አጥ መታወቂያ ካርድ፣
  5. የአባላቱ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ፣
  6. የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሁለት ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶ ግራፍና ከማህበሩ አባላት የተወከለበት የውክልና ማስረጃ ማቅረብ 
  7. የፀደቀ የንግድ ስም ስያሜ ማስረጃ፣
  8. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ፣
  9. የአዋጭነት የንግድ ስራ እቅድ ማቅረብ፣
  10. በውልና ማስረጃ የጸደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ፣
  11. በሚዘጋጀው የምዝገባ ቅጽ ላይ የንግድ ስራ አድራሻውን በመሙላትና በፊርማው በማረጋገጥ ማቅረብ የሚችል፣
  12. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው የስራ መስኮች) 
  13. የማህበሩ የቁጠባ/የተንቀሳቃሽ ሂሳብ ከፋይናንስ ተቋማት ስለመከፈቱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ 

    2.3 ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበርመስፈርቱም 

  1. በጥቃቅንና አነስተኛ ለመደራጀት ለአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የቀረበ ጥያቄ
  2. የማህበሩ አባል ለመሆን የቀረበ የግል ማመልከቻ ከሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር ማቅረብ 
  3. የማህበር መመስረቻ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ የሚችል
  4. የስራ አጥ መታወቂያ ካርድ፣
  5. የአባላቱ የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ፣
  6. የፀደቀ የንግድ ስም ስያሜ ማስረጃ፣
  7. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ፣
  8. የአዋጭነት የንግድ ስራ እቅድ ማቅረብ፣
  9. በውልና ማስረጃ የጸደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ፣
  10.  በሚዘጋጀው የምዝገባ ቅጽ ላይ የንግድ ስራ አድራሻውን በመሙላትና በፊርማው በማረጋገጥ ማቅረብ የሚችል፣
  11.  የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው የስራ መስኮች) 

     12) ሺህ ብር ከፋይናንስ አቅራቢ ተቋም