የሥራ ሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት
የሥራሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
- የተቋሙ ፖሊስዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ኮንቬንሽኖች፣ መርሀ-ግብሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና፣ የአድቮኬሲ አገልግሎት መስጠት፤
- የሰው ኃይል አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት መሰረት ያደረገ የተሟላና ወቅታዊ የሥራ ገበያ መረጃዎችንተደራሽ ማድረግ፣
- ዜጎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸዉ በፊትና በስራ ላይ እያሉ ከስራ ባህልና አጠቃላይ ከስራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
- በክልል ዉስጥና ከክልል ዉጪ በሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀይል ጥያቄ ተቀብሎ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ነፃ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት፣
- ሥራ አጦችንና ሥራ ፈላጊዎችን፣ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የመመዝገብ አገልግሎት፣
- ለአገር ዉስጥ እና ለዉጭ አገር የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የቅድመ ፈቃድ /የቅርንጫፍ ፈቃድ/ እድሳት ቁጥጥር፣ ክትትል ድጋፍ አገልግሎት፣
- ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ዜጎች በቴክኒክ ሙያ የክህሎት ሥልጠና የድጋፍና ክትትል እና የቅድመ-ጉዞ ትምህርትና ስልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
- ለሥራ አጦችና ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ-ሥራ ሥምሪት ሥልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
- የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን መከላከል፣
- የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት