Vocational training and enterprises support service
Link text or object
Link text or object
Link text or object
1. የሠልጣኝ፣ አሠልጣኝና አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
በሥራ ገበያ ፍላጎት ጥናት መሠረት ገበያ ተኮር ሥልጠና መሥጠት፣
የኢትዮጵያ የሙያ ደረጃን ለአሰልጠኝ ኮሌጆች ከፌደራል በመውሰድ ማሰራጨት፣
ስርአተ ትምህርትና ቲቲኤልኤም በማዘጋጀት ሥልጠና መሥጠት፣
የትምህርት ስልጠና መሳሪያዎችን ለማሰልጠኛ ተቋማት ማቅረብ ፣
በኩባንያና ኢንዱስትሪ ውስጥ የትብብር ስልጠና ማስተባበር፣
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሴቶች፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች እና የገጠሩ ማህበረሰብ አባላት በተመጣጣኝ ተሳትፎ ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ፣
የድህረ-ሥልጠና ክትትል ጥናት ማድረግ፣
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆች የሥልጠና ስታንዳርድ ማዘጋጀት፣ (የሰው ኃይል፣ የፊዚካል ፋሲሊቲና የሥልጠና መሳሪያዎች) ማዘጋጀት ፣ ማቋቋም፣ ማስፋፋት፣ ማስተዳደርና ስታንዳርዱን ማስጠበቅ፣
ለመንግስት፡ለግልና መያድ ማሠልጠኛ ኮሌጆች የፕሮግራም ምዝገባ፣ የዕውቅናና የማስፋፊያ ፈቃድ መሥጠትና ማደስ፣
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች(መደበኛ፣ ኢ-መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ) ስኬታማ እንዲሆኑ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ፣
ጥራቱን የጠበቀ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መስጠት፣
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሥራ ኃላፊዎችና አሠልጣኞች የብቃት መሥፈርት ተግባራዊ ማድረግ
ችግር ፈች የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማዘጋጀት ለኢንተርፕራይዞች ማሸጋገር
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ መሥጠት፣
የዘርፉን ልማት ለማፋጠን ሀብት በማፈላለግ የሥልጠና ግብዓት ማቅረብ፣
2) የተቋማት አቅም ግንባታና የሥልጠና ጥራት ማረጋገጫዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
መስፈርቱን ላሟሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት እውቅና ፈቃድ መስጠት፣
ስልጠናቸውን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ለተከታተሉ ሰልጣኞችና በተለያዩ ምክንያት ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ግለሰቦች የስልጠና ማስረጃ ማረጋገጥ፣
በመንግስት ኮሌጆች/በማሰልጠኛ ተቋማት/ የግንባታ ፍላጎት መለየትና ማቋቋ፣
በየኮልጁና ተቋማት የማሽን ፍላጎት በማጥናት ማሽነሪዎች እዲሟሉ ማድረግ፣
ለተቋማት ድጋፍ በመስጠት፣ ክትትል በማድረግና ግብረ መልስ በመሥጠት የሥልጠና ጥራት ማስጠበቅ፣
የት/ሥ/ ጥራት ለማሻሻል የሚረዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማካሄድ፣ ለት/ሥ/ተቋማት በሥልጠና ዕውቅና ፈቃድ አሰጣጥ የምክር አገልግሎት መሥጠት