ለ ኢንተርፕራይዞች ምርት የገበያ ትስስር መፍጠር ለኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተገለፀ ።
ደቡባዊ ሲዳማ ዞን ለ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ባዛርና ኤግዚቢሽን መክፈቱን የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ገለፀ ።
በመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የተገኙት ሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር ማቴ መንገሻ ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥተው እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀው ክህሎትን መሠረት ያደረገ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በተሰጠው ትኩረት ኢንተርፕራይዞች የራሳቸውን ሀብት ከማፍራት አልፈው ለሌሎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ተናግሯል ።
ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ ለምርታቸው የገበያ ትስስር ለመፍጠር በሚዘጋጁ ባዛርና ኤግዚቢሽን ተጠቃሚነታቸው እያደገ መጥቷልም ብሏል።
በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንገሻ ፊታሞ በበኩላቸው ለወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቅድሚያ ተሰጥተው እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ለምርታቸው የገበያ ትስስር በመፍጠር ውጤታማ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልጿል ።