የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሁለተኛ ዙር የድጋፍ ክትትል ስምሪት ዙሪያ ለአመራሮችና ለሠራተኞች የኦሬንቴሺን መድረክ አካሄደ ።
የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የሁለተኛ ዙር በዘመቻ ለአንድ ወር የሚቆይ ከዞን እስከ ወራዳና ቀበሌ ድረስ የድጋፍ ክትትል ስምሪት ዙሪያ ለአመራሮችና ለሠራተኞች የኦሬንቴሺን መድረክ አካሄደ ።
በመድረኩ ላይ የቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በመጀመሪያ ዙር በዘመቻ ሥራ በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት ለማምጣት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል ።
በተጨማሪም በሁሉም ዙር የሁሉም ዘርፍ የቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በማቀናጀት እስከ ቀበሌ ድረስ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የካቲት 17/2017 ጀምሮ ለተከታታይ 30ቀናት የሚቆይ ስምሪት የጋራ ስምምነት በመፍጠር አሰማርተዋል ።