ችግር ፈቺ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራ የተፈለገውን ውጤት ለማምጣት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ተገለፀ ::
የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማምጣትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ 2ኛ ዙር በዘመቻ ድጋፍና ክትትል ከዞን ፣ ወረዳና እስከ ቀበሌ ድረስ ለ30 ተከታታይ ቀናት የሚቆየውን ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አመራርና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደዋል ።
በዘመቻው በትኩረት ከሚሰሩ ጉዳዮች መካከል አጫጭር ገበያ ተኮር ስልጠና ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ፣ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዙሪያ፣ የአንድ ማዕከል ግንባታ ጉዳይ፣ ኢንተርፕራይዞችን በባዮሜትሪክስ የመመዝገብ ስራ፣ 5 ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ሥለጠና ዙሪያ፣ ብሔራዊ መታወቂያና በመደበኛ ሥራዎችን መሆኑን ተገልጿል ።