ወጣቶችን በክህሎትና የኢኮኖሚ አቅማቸውን በመገንባት በቢዝነሳቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ከአጋር ተቋማት ጋር በተሰራ ስራ ውጤት መምጣቱ ተገለፀ።
HELVETAS UP-WOMEN መንግስታዊ ያልሆነ ፕሮጀክት ከሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመቀናጀት የስራ እድል የተፈጠረላቸውን 19 የሴት ኢንተርፕራይዞችን የቢዝነስ ሀሳባቸዉን በማወዳደር አሸናፊ ለሆኑ ለዘጠኝ ኢንተርፕራይዞች 1.8 ሚሊዮን ብር በሽልማት አበረከተላቸው ።
በመድረኩላይ የተገኙ የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ HELVETAS UP-WOMEN ፕሮጀክትሴት ወጣቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከቢሮዉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በርካታ ዉጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
ቢሮውሴቶች መስራት አይችሉም የሚለውን አስተሳሰብ በመቀየር በብዙዎች የማይደፈሩ ጠጣር ሙያዎችን በማሰልጠን የስራ ባለቤት እንዲሆኑና በክህሎታቸውና በቢዝነሳቸው ተወዳዳሪ የሚሆኑትን ማፍራት ተችሏል ያሉት ወ/ሮ ሀገረጽዮን ለፕሮጀክቱ ምስጋናቸውን በማቅረብ በዛሬው እለት ተወዳዳሪ ሆነው የሚያሸንፉት ሴቶች ከስራቸው ተሽለው የተገኙ በመሆናቸው ከሽልማቱ በሚያገኙት ገንዘብ ቢዝነሳቸውን ማስፋት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።