ከፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒሰትር ድኤታ ክቡር አቶ ስለሞን ሶካ የተመራው የድጋፍና ክትትል ቡድን በሲዳማ ክልል ለአንድ ሳምንት ሲያካሂድ የቆየውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናቋል ።
ከ ክህሎት ልማት ፣ ከስራ እድል ፈጠራና ከኢንዱስትሪ ሠላም ስራዎች አንፃር በክልሉ መልካም ተሞክሮ የሚሆኑ በርካታ ስራዎችን ማየት ችለናል ሲሉ የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒሰትር ድኤታ ክቡር አቶ ስለሞን ሶካ ገለፁ።
ቡድኑ በቆይታቸው በዘርፉ የተሰሩ በርካታ ስራዎችን ወደ ታች በመውረድ ተዘዋውሮ የተመለከቱ ሲሆን ከክህሎት ልማት ፣ ከስራ እድል ፈጠራና ከኢንዱስትሪ ሠላም ስራዎች አንፃር በክልሉ ተሞክሮ የሚሆኑ በርካታ ስራዎችን ማየት መቻላቸውን ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ስለሞን ሶካ ገልጸዋል ።
አቶ ሰለሞን አክለውም ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሲዳማ አልፈው ለአፍሪካ የሚሆን እምቅ አቅም ያለው መሆኑን ማየት ችለናል ብለዋል።