Skip to main content

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ ሱፐርቪዥን ቡድን በሲዳማ ክልል ድጋፍና ክትትል ማካሄድ ጀመረ።

image news

ወደ ክልሉ የመጣውን የሱፐርቪዥን ቡድን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በቢሯቸው የተቀበሉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በክልሉ ውስጥ በየዘርፉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና የዚህም ሴክተር ስራ በልዩ ትኩረት እየተደገፈና እየተመራ ያለ መሆኑን በማንሳት የተሰሩ ስራዎችን ቡድኑ በሁሉም አካባቢዎች ተዘዋውሮ እንዲመለከት ጋብዘዋል።

ቡድኑ በቆይታው በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት የተሰሩ ሥራዎችን ከቢሮው ጀምሮ በየደረጃው በሚገኙ ኮሌጆች፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት፣ ኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪዎች ላይ ምልከታ የሚደርጉ ይሆናል፡፡