ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሠራ ነው፡፡
ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ገለፀ ።
ቢሮው ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ማልጋ ወረዳ በመንግሥት ድጋፍ በተለያዩ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ጉብኝት በማድረግ ከወረዳ አመራሮች ጋር የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል ።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ቅድሚያ በመስጠት በተሠራው የወጣቶች ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ።
ወጣቶች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የተፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ክህሎትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በመስጠት ወጣቶች በተሰማሩበት ስራ መስክ ይበልጥ ውጤታማ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል ።