በክልሉ በአፈጻጸም ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ቡድኑ ያመጣውን ግብረ መልስ ተቀብለን የተለዩ ጉዳዮችን ለማሻሻል በትኩረት ይሠራል :-ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ
የሲዳማብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢፌደሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለድጋፍና ክትትል ከመጣው ቡድን ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሲዳማ ክልል የ2018 የበጀት አመት የ6 ወራት አፈጻጸም የሱፐርቪዥን የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ሪፖርት አቅርበዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ በአፈጻጸም ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ቡድኑ የመጣውን ግብረ መልስ ተቀብለን በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አክለውም ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ እድል ፈጠራ፣ ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት አንጻር እንዲሁም ከተቋም ግንባታ አንፃር የቀረቡ ጉዳዮች አፈጻጸም በጥንካሬና እንዴ ተሞክሮ መቅረቡን ጠቁመው በቀጣይም የሚደረግ አሰፈላጊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።