Skip to main content

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አዘጋጅነት በለኩ ከተማ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር የታለመ ኤግዚቢሽን በይፋ ተጀምረ።

image news

በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አዘጋጅነት በለኩ ከተማ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠር የታለመ ኤግዚቢሽን በይፋ ተጀምረ።

በለኩ ከተማ በይፋ በተከፈተው የኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን ላይ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደረሰ ፣ የለኩ ከተማ ከንቲባ አቶ ፀጋዬ አባተ ፣ የለኩ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታደለ እንዲሁም የዞን እና የከተማው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በኤግዚቢሽኑ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተገኘዉ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደረሰ "ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ በዛሬው እለት በለኩ ከተማ በይፋ ያስጀመርነዉ የኤግዚቢሽን መድረክ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።" ብሏል።