Relaxing Porn Videos
የሲዳማ ክልል ልዑክ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ማካሄድ ጀመረ። | Sidaama National Regional Staten skill & Enterprises Development Bureau Skip to main content

የሲዳማ ክልል ልዑክ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ማካሄድ ጀመረ።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥራና ክህሎት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ ማካሄድ ጀምሯል።

የልምድናተሞክሮ ልውውጥ መድረኩ የእንኳን በደህና መጣችሁ አቀባበል በማድረግ የተጀመረ ሲሆን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እንደገለፁት ልዑኩ የመጣበት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ24/7 አዲስ የስራ ባህል ተፈጥሮ አስደናቂ ውጤት እያመጣ በሚገኝበት ጊዜ መሆኑ ለልምድ ልውውጡ መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል።

አቶሚሊዮን በተጨማሪም በቢሮው እየተተገበረ ያለው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ስራ ለሌሎች ክልሎች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።