Skip to main content

የሲዳማ ክልል የፖለቲካ አመራሮች በሥራ እድል ፈጠራ ስራ ላይ የሰጠው ትኩረት ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው::

image news

የሲዳማ ክልል የፖለቲካ አመራሮች በሥራ እድል ፈጠራ ስራ ላይ የሰጠው ትኩረት ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ገለፁ

በክልሉ በሁሉም ዞኖች የገጠር ሥራ እድል ፈጠራ ሥራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሚመራው የድጋፍና ክትትል ቡድን ለአራት ተከታታይ ቀናት እያደረጉ የቆዩትን ድጋፍና ክትትል ጨረሰው ግብር መልስ በሰጡበት ገልጸዋል ።

ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች ከሪፖርት ባሻገር ያሉበትን የአፈፃፀም ሁኔታ በመመልከት ችግሮችን ለመፍታትና አፈፃፀሙን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ዶ/ር ተሻለ አንስተዋል ።