ስራን ሳይንቁ መንግሥት ያመቻቸላቸው እድል መጠቀም የቻሉ ወጣቶች ከሰው እጅ ከማየት የራሳቸውን ሀብት ማፍራት ችለዋል።
የሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ ወጣቶች መንግስት ያመቻቸውን እድል ተጠቅመው በኢንተርፕራይዝ ተደራጅተው ሀብት ማፍራት የቻሉትን የስራ እንቅስቃሴ ጉብኝት ማድረጋቸውን ቢሮ ገለፀ
በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ጨምሮ የቢሮ ምክትል ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት በመገኘት ወጣቶች ተደራጅተው በመስራት የራሳቸውን ሀብት ከማፍራት ባሻገር ለሌሎች የስራ እድል መፍጠር መቻላቸውን ማየት ተችሏል ።