የሲዳማ ክልል ምክርቤት የከተማና መሠረ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ 2017 በጀት አመት የሥራና ክህሎት ቢሮ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርተር ገመገሙ ።
የሪፖርቱ ግምገማ መድረክ የመሩት የሲዳማ ክልል ምክርቤት የከተማና መሠረት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ ክብረት ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/መሰቀል ቢሮው የአመቱ እቅድና ትግበራ በጥልቀት የገመገሙ ስሆን በግምገማው በአመቱ የታዩ ውጤቶች ተሰፋ የሚሰጥና በሁሉም ዘረፍ ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉ መየት ችለናል በለዋል ።
በተጨማሪም ቢሮው በአመቱ ውስጥ የሰራውን አመርቂ ስራ አጠናክሮ መቀበል እንዳለበት እንደሁም የዘርፉን ውጤት ለበለጠ ለማጠናከርና የዜጎቻችን ችግር ለመፍታት አድስ ስልት በመቀየስ የተሻለ እቅድ ማቀድ እንዳለበት ተጠቁሟል ።
በመቀጠል የሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው የቢሮው የ2017 በጀት አመት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት ስሆን ፤ በአመት ውስጥ ቢሮ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።