የቢሮ ኃላፊ መልዕክት


ሀገረፅዮን አበበ

የስራ ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ስ/ክ/ኢ/ል/ቢሮ እንደ ቢሮ የተቋቋመው በ2014 ዓ.ም ሲሆን ሶስት ዋና ዋና ዘርፎችን ማለትም የሙያ ስልጠና እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍን፣ የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍን እና አሰሪና ሰራተኛ ልማት ዘርፍን አካቶ በመያዝ ለክልሉ ብሎም ለሀገር አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶአል፡፡

አሰሪና ሰራተኛ ልማት ዘርፍ ከስራ፣ ከሰራተኛ ገበያ መረጃ፣ ከኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲሁም ከስራ ደህንነትና ከጤና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሃላፊነትን ወስዶ ይሰራል።በአሰሪና በሰራተኞች መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአሰሪ፣ በሠራተኛና በመንግሥት መካከል ያለውን የሦስትዮሽ ግንኙነትን የማጠናከር ተግባራትን ያከናውናል፡፡ የግሉ ሴክተር የአሰሪና የሠራተኛ ግንኙነት ለመምራት የወጡ ፖሊሲዎች እና የሕግ ማዕቀፎች በክልሉ ተግባራዊ መሆናቸውን በበላይነት ይከታተላል፡፡

ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለአንድ ሀገር ክህሎት፣መልካም አመለካከት እና እውቀት ያላቸውን ወጣቶች የማፍራት ዓላማ ያለው የትምህርት ስርዓት አካል ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት TVETን ለኢኮኖሚ ዕድገትና ሥራ አጥነትን ለመቀነስ ዋና መሳሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

ዜናዎች

ከ ክህሎት ልማት ፣ ከስራ እድል ፈጠራና ከኢንዱስትሪ ሠላም ስራዎች አንፃር በክልሉ መልካም ተሞክሮ የሚሆኑ በርካታ ስራዎችን ማየት ችለናል ሲሉ የፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒሰትር ድኤታ ክቡር አቶ ስለሞን ሶካ ገለፁ።

ከፌዴራል የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የመጣው የድጋፍና ክትትል ልዑካን ቡድኑ ከ ክህሎት ልማት አንፃር የተሰሩ ስራዎችና የስራ እድል ፈጠራ በኩል የተሰሩ ስራዎች በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በቦርቻ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ውስጥ እየተሰራ ያሉ ስራዎችን ፣ ወንዶ ገነት ወረዳና ወንዶ ገነት ከተማ ውስጥ የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን ተመልክቷል ።

ወደ ክልሉ የመጣውን የሱፐርቪዥን ቡድን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በቢሯቸው የተቀበሉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በክልሉ ውስጥ በየዘርፉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና የዚህም ሴክተር ስራ በልዩ ትኩረት እየተደገፈና እየተመራ ያለ መሆኑን በማንሳት የተሰሩ ስራዎችን ቡድኑ በሁሉም አካባቢዎች ተዘዋውሮ እንዲመ

ኃላፊዎች

ፍስሀ ፍቾላ ባኩሎ

የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የሙያ ስልጠና እና ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ

ከፍያለው ከበደ

የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የሥራ እድል ፈጠራ ልማት ዘርፍ ኃላፊ

ዶ/ር ማቴ መንገሻ

የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና አሠሪና ሠራተኛ ልማት ዘርፍ ኃላፊ

አዝመራ አመኖ

የቢሮ ምክትል ኃላፊ ማዕረግ የአስተዳደር እና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ

ስለሺ ሱራፌል ጤካሞ

የግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

ብርሃኑ ያዕቆብ

የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር