የተቁዋም አቅም ግንባታ የስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት
በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት ከተገልጋዮች የሚጠበቀው
- ማግኘት የሚፈልጉትን አገልግሎት መለየትና በተዘጋጀው ቅጽ ላይ መሙላት
- የተገልጋዩ ስምና አገልግሎቱን ያገኙበትን የጊዜ እርዝማኔ በተዘጋጀው መዝገብ ላይ ማስፈር
- ከአገኙት አገልግሎት መነሻ የእርካታ ደረጃ በተዘጋጀው ካርድ መግለጽ
የትምህርት ማስረጃ እንዲረጋገጥላችሁ የምትመጡ ተገልጋዮች
- የትምህርት ማስረጃው በጀርባው ላይ የኮሌጁ ኃላፊና ሬጅስትራር ፊርማና ማህተም መኖር አለበት
- በኮሌጅ ኃላፊና ሬጅስትራር የተፈረመና ማህተም ያረፈበት ኦሪጅናልና ኮፒ የትምህርት ማስረጃ
- የስም ለውጥ ካለ የፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈበት ማስረጃ
- በሌላ ሰው ለማስረጋገጥ የሚላኩ ማስረጃዎች ካሉ በፍርድ ቤት የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ መቅረብ አለበት