Skip to main content

Employer and employee development sector

1. ሰላማዊ የኢንዳስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትየሚሰጡ ዋናዋና አገልግሎቶች    

  • የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የህግ ማዕቀፎችና የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣
  • የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የህግ ማዕቀፎች፣ፖሊሲዎች፣ደንቦች፣መመሪያዎችና ኮንቬንሽኖች በተመለከተ በአሰሪዎች፣ሠራተኞችና የሚመለከታቸው አካላት  ዘንድ ንቃተ ህግ እንዲፈጠር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠናዎችንና የአድቮከሲ ሥራዎችን ማካሄድ፣
  •  የሥራ አካባቢዎችና የሥራ ሁኔታዎችን ለማሻሻል የሚረዱ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና ሥራ አካባቢ ጥበቃንና የመሠረታዊ ሥራ ሁኔታዎች አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ጥምር የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥሮችን ማካሄድ፣
  • በመከላከል፣ከለላ በመስጠትና በመልሶ ማቋቋም መርህ ላይ በመመስረት በድርጅቶች ውስጥ አስከፊ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን መቆጣጠር፣ መከታተል፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
  • በድርጅቶች የሙያ ደህንነትና ጤንነት አመራር ሥርዓትን መዘርጋትና  የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
  • በሙያ ደህንነትና ጤንነት ዘርፍ በማመከር አገልገሎት ለሚሠማሩ የግል ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት፣
  • የሥራ ቦታ ትብብርና የማህበራዊ ምክክር ስርዓትን በድርጅት ደረጃ መዘርጋትና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
  • በአሠሪና በሰራተኞች መካከል የሚከሰቱ የሥራ ክርክሮችን በማስማማት እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በዳኝነት አገልግሎት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ፣ 
  • አሠሪዎችና ሠራተኞች ጥቅሞቻቸውንና መብቶቻቸውን ለማስከበር በህግ የተሰጣቸው በማህበር የመደራጀትና የህብረት ድርድር የማድረግ መብቶቻቸው መከበራቸውን ለማረጋገጥ መከታተልና ድጋፍ ማድረግ፣
  • የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራትንና የህብረት ሥምምነትን መመርመር፣ መመዝገብና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፣
  • የሥራ ሁኔታዎች መቆጣጠሪያ አገልግሎትን የማስፈጸም አቅምና የቴክኒካዊ የብቃት ደረጃ ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዱ የማቴሪያልና የባለሙዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማካሄድ፣ 

2. የሥራ ሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የተቋሙ ፖሊስዎች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች፤ ኮንቬንሽኖች፤ መርሀ-ግብሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና፤ የአድቮኬሲ አገልግሎት መስጠት፤
  • የሰው ኃይል አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት መሰረት ያደረገ የተሟላና ወቅታዊ የሥራ ገበያ መረጃዎችንተደራሽ ማድረግ፣ 
  • ዜጎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸዉ በፊትና በስራ ላይ እያሉ ከስራ ባህልና አጠቃላይ ከስራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
  • በክልል ዉስጥና ከክልል ዉጪ በሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀይል ጥያቄ ተቀብሎ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ነፃ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት፣
  • ሥራ አጦችንና ሥራ ፈላጊዎችን፣ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የመመዝገብ አገልግሎት፣
  • ለአገር ዉስጥ እና ለዉጭ አገር የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የቅድመ ፈቃድ/የቅርንጫፍ ፈቃድ/እድሳት ቁጥጥር፣ ክትትል ድጋፍ አገልግሎት፣
  • ወደ ውጭ አገር  ለሚሄዱ  ዜጎች በቴክኒክ ሙያ የክህሎት ሥልጠና የድጋፍና ክትትል  እና የቅድመ-ጉዞ ትምህርትና ስልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
  • ለሥራ አጦችና ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ-ሥራ ሥምሪት ሥልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
  • የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን መከላከል፣
  • የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት