የሥራ ሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት
የሥራሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
- የተቋሙ ፖሊስዎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ኮንቬንሽኖች፣ መርሀ-ግብሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና፣ የአድቮኬሲ አገልግሎት መስጠት፤
- የሰው ኃይል አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት መሰረት ያደረገ የተሟላና ወቅታዊ የሥራ ገበያ መረጃዎችንተደራሽ ማድረግ፣
- ዜጎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸዉ በፊትና በስራ ላይ እያሉ ከስራ ባህልና አጠቃላይ ከስራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
- በክልል ዉስጥና ከክልል ዉጪ በሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀይል ጥያቄ ተቀብሎ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ነፃ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት፣
- ሥራ አጦችንና ሥራ ፈላጊዎችን፣ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የመመዝገብ አገልግሎት፣
- ለአገር ዉስጥ እና ለዉጭ አገር የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የቅድመ ፈቃድ /የቅርንጫፍ ፈቃድ/ እድሳት ቁጥጥር፣ ክትትል ድጋፍ አገልግሎት፣
- ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ዜጎች በቴክኒክ ሙያ የክህሎት ሥልጠና የድጋፍና ክትትል እና የቅድመ-ጉዞ ትምህርትና ስልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
- ለሥራ አጦችና ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ-ሥራ ሥምሪት ሥልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
- የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን መከላከል፣
- የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት
የሥራ ስምሪት ዳይሬክቶሬት የሀገር ውስጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ፈቃድ ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶቸ
- የስራ ፈቃድ ለማውጣት በጽሁፍ የቀረበ የጥያቄ ማመልከቻ፡
- የንግድ ፈቃድ እናየንግድ ስምምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤
- የአመልካቹ የስራ ቦታአድራሻና የቢሮ ይዞታ የራስ ከሆነ የባለበትነትማረጋገጫ ደብተር ወይም ኪራይ ውልበሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ዋናቅጂ
- የሚከፈተው ቢሮ ከዋናው መንገድ 100 ሜትር በላይ ያልራቀ እናየዋናው ቢሮክፍል ስፋት ቢያንስ 16 ካሬ ሜትር፤የተገልጋዮችማስተናገጃ ክፍል 20ካሬ ሜትር በጠቅላላው የቢሮ ስፋት 36 ካሬሜትር ሆኖለተገልጋዮች መቀመጫ ቢያንስ 12 ወንበሮች ያሉት መሆን አለበት፤
- ደረጃውን የጠበቀ ቢሮየአደረጃጀት መዋቅሩን የምያሳይ ቻርት፤
- የሰው ሀይል አደረጃጀቱ በኤጄንሲው ቢሮ ደረጃ በተመለከተ፤
- የኤጀንሲው ስራአስካያጅ፤
- ጉዳይ አስፈፃሚ፤
- የሪከርድና የማህደር ሠራተኛ፤
- ቅድመ ቅጥር ገለፃና ምክር አገልግሎት ባለሙያ
- ለስራ የሚያስፈልግ የሰው ሀይል ዝርዝርና የትምህርት ማስረጃ የእያንዳንዱ ሰራተኛ የስራ መደብና የስራ መዘርዝር፤የግልታርክ፤ የፓስፖርት መጠን ያላቸው ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፎች መኖር አለበ
- ስራ አስኪያጁ ቢያንስ የኮለጅ ድፕሎማ ኖሮት በማህበራዊ ሳይንስ (በሕግ) የትምህርት መስክ ድፕሎማ እና 5 ዓመት የስራ ልምድ ፤ ድግር ከሆነ የ3 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ ያላት ስለመሆኑ/ዋ የሚገልጽ ማስረጃ እናቀደም ሲልከምሰሩበት መ/ቤት የስራ መልቀቅያ (ክሊራንስ) ማቅረብ የምችል/የምትችል፡፡
- 4ቱም ሠራተኞች የቅጥር ደብዳቤ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ዋና ቅጅ
- 4ቱም ሠራተኞችና የኤጀንሲው ባለበት ማንነትን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ
- ሁሉም የምቀርብ መረጃ ከምቀርብበትከተማ/ወራዳ ሠ/ማ/ጉ/መምሪያ /ጽ/ቤት ጉዳዩ የሚመለከተው አስተባባር/ባለሙያ መረጃ ትክክለኛ ስለመሆኑ በቲቴር የተረጋገጠ መሆን አለበት
- 4ቱም ሠራተኞች የተቀጠሩበት ደመወዝ ለመንግስት ግበር ለመክፈል የሚያበቃ መሆኑን ማረጋገጥ
- ኤጀንሲው የተከራየበት ቢሮበተራ ቁጥር አራት (4) በተቀመጠው መስፈርት መሰረት መሆኑን የኤጀንሲውን መረጃ አጣርቶ ወደክልል የሚልከው አካል ማጣራቱን የሚያስይ በአስተባባሪ/ባለሙያ ፊርማና በማህተም ተረጋግጦ መላኩን ማረጋገጥ.
- የኤጀንሲው ባለቤት፣አመራር አባላት እና ሠራተኛች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጅል ያልተቀጡ እናከማንኛውም ወንጅል ነፃ ሰለመሆናቸው የሚያረጋገጥ የፖሊስ ማሰረጃ
- አመልካቹ የንግድ ማህበር ከሆነ በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የማህበሩ መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ዋናቅጂ ከኮፒ ጋር.
- በሕግ የተወሰነ የፈቃድ አገልግሎት ክፍያ የተከፈለበት ደረሰኝ.
- አመልካቹ በቅድመ-ፈቃድ ገለፃ ሰለመሳተፉ አግባብ ካለው ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት.
- ስለ ምዝገባና አመላመል ስነ-ሥርዓት
- ማንኛውም ኤጀንሲ ሥራከመጀመሩ በፊት የሥራ ፈላጊ አመልካቾች ምዝገባና የአመላመል ሥነ-ሥርዓት የአሰራር መመሪያ አዘጋጅቶ ማቅርብ አለበት
- ስለዋስትና ገንዘብ እናኢንሹራንስ
- ከሰራተኛ ጋር የሥራ ውል በመፈጸም ሠራተኛውን ለአገልግሎት ተጠቃሚ ድርጅት በማቅረብ የሚሰራና የሚያስተዳድር ኤጀንሲ ለሰራተኛው መብት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል የሚከተለውን የገንዘብ መጠን በባንክ በዝግ ሂሳብ ማስቀመጥ አለበት፤
- እስከ 100 ለሚደርሱ ሠራተኞች 100ሺየኢትዮጵያ ብር፤
- እስከ 101-500 ለሚደርሱ ሠራተኞች 250ሺየኢትዮጵያ ብር፤
- እስከ 500 በላይ ለሚደርሱ ሠራተኞች 350ሺ የኢትዮጵያ ብር፤