በሰልጣኝ፣ አሰልጣኝና አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት
ሰትራቴጅክ ግብ 1፡- ተቋማዊ አቅምና ብቃት ማሳደግ፤
ተቋማዊ አቅምና ብቃት ከማሳደግ አንፃር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤
- የአሰልጣኞችና የመዛኞች ልማት ማጠናከርና ማስፋፋት
- ተከታታይ የአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ማከናወን
- ለ አሰልጣኞች የሙያ ፈቃድ መስጠት
- የአሰልጣኞች የስልጠና ፍላጎት/ክፍተት ለመለየት የዳሰሳ ጥናት ማድረግ
- ለአሰልጣኞች በአጫጭር ስልጠና የሙያ ማሻሻያና የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት
- በቴ/ሙ/ስ/ተቋማት አሰልጣኞች ላይ የጥራት ማረጋገጫ ኦዲት ማከናወን
- አሰልጣኞችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሶስተኛ ዲግሪ ማሰልጠን
- አሰልጣኞችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሁለተኛ ዲግሪ ማሰልጠን
- አሰልጣኞችን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ ማድረግ
- የአሰልጣኞች እና አመራሮች የብቃት ማዕቀፍ ማሻሻል
- በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኞችና የፈጠራ ባለሙያዎች የሽልማት መርሃ ግብር ማዘጋጀትና የአሰልጣኞች የጥቅማ ጥቅም ሥርዓት መዘርጋት
- የውጭ ሀገር አሰልጣኞችን በቅጥር ወይም በበጎ ፍቃደኝነት በማሰልጠንና በቴክኖሎጂ ስራ ላይ ማሰማራት
- የሰልጣኞች ቁጠባ አገልግሎት ስርዓት መዘረጋት
- መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋትና የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እውቅና እና ማበረታቻ መስጠት
ስትራቴጅክ ግብ፡- 2 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትና አግባብነት ማሳደግ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትና አግባብነት ከማሳደግ አንጻር የሚከናወኑ ተግባራት
- ለትብብር ስልጠና ተባባሪ ለሆኑ ኢንዱስትሪዎች የማበረታቻ ደንብ ማዘጋጀት
- ሰልጣኞችን በትብብር ስልጠና ማሳተፍ
- ሰልጣኞች በሙያ ጋይዳንስና ካውንስሊንግ አገልግሎት ተጠቃሚ አንዲሆኑ ማድረግ
- ለስልጠና አጠናቃቂዎች በማሰልጠኛ ተቋማት የስራ ትውውቅ እድል ማመቻቸት
- የስልጠናውን የተግባርና የንድፈ-ሃሳብ ሚዛኑን በመጠበቅ የሰልጣኞች ሙያ ብቃት፣ ስነ-ምግባርና እሴቶች እንዲዳብር ማድረግ
- በሰልጣኞችና የአሰልጣኞች ስነ ምግባር ደንብ በማዘጋጀት እንዲሻሻል ማድረግ
- የሰልጣኞች የበጎ ፍቃድና ብሄራዊ አገልግሎት ማስፈጸሚያ ሥርዓት መዘረጋት
- የሰልጣኞችን ብቃት ለማረጋገጥ ትክክለኛ፣ አስተማማኝና አካታች የሆነ የምዘና ስርዓት መፍጠርና ማጠናከር
- የስልጠናውን ጥራት ለማስጠበቅ ከኢንዱስትሪው ጋር በጋራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
- የመደበኛና በገበያ-ተኮር አጫጭር ስልጠና የስልጠና አጠናቃቂዎች በሙያ ብቃት ምዘና የመብቃት ምጣኔ ማሳደግ
- የስልጠና ጥራትን ለመጠበቅና ለማጠናከር በቂ ግብዓትና አቅርቦት እንዲሟላ ማድረግ
- የሰልጣኞች የምልመላ መስፈርት ማዘጋጀት
- በጋራ ቅጥር የሚሰሩ የኢንደስትሪ ባለሙያዎች / የተቋም አሰልጣኞች ማፍራት
ስትራቴጅክ ግብ 3 የቴክኒክናሙያ ስልጠና ተደራሽነትና፣ ፍትሐዊነትን ማሳደግ
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተደራሽነትና፣ ፍትሐዊነትን ከማሳደግ አንጻር የሚከናወኑ ተግባራት
- የስልጠናውን ፍትሃዊነት ማረጋገጥ
- በሰልጣኞች የሙያ መረጣ ኢንዱስትሪዎች ሙያዊ ማብራሪያ የሚሰጡበት ስርዓት መዘርጋት
- ውጤታማ ሴት ኢንተርፕራይዞች ተሞክሮ ተቀምሮ ለሴት ሰልጣኞች የሚሰፋበትን አሰራር መዘረጋት
- በመደበኛ መርሃግብር ወደ ቴ/ሙ/ስ/ የሚገቡ ነባር ሰልጣኞችን ቁጥር ማሳድግ
- በመደበኛ መርሃግብር ወደ ቴ/ሙ/ስ/ ከሚገቡ ነባር ሰልጣኞች የሴት ሰልጣኞችን ድርሻ ማሳደግ
- በመደበኛ መርሃግብር ወደ ቴ/ሙ/ስ/ የሚገቡ አዲስ ሰልጣኞችን ቁጥር ማሳድግ
- በመደበኛ መርሃ ግብር ወደ ቴ/ሙ/ስ/ ከሚገቡ አዲስ ሰልጣኞች የሴት ሰልጣኞችን ደርሻ
- በአጫጭር ስልጠና ወደ ቴ/ሙ/ስ የሚገቡ ሰልጣኞችን ቁጥር ማሳደግ
- ሴት ሰልጣኞች ትኩረት ወደሚሹ ሙያዎች ገብተው እንዲሰለጥኑ የተዘረጋ የማበረታቻ ስርዓት መዘርጋት
- የሴቶች እና ልዩ ፍላጎቶት ላላቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ መመሪያ ማተዘጋጀት
- ልዩ ችሎታ/ተሰጥኦ ያላቸው ሰልጣኞች በመለየት ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰራር ስርአት መዘረጋት
- በመደበኛ ስልጠና መርሃ ግብር ሰልጠና ያገኙ ልዩ ፍላጎት ያላቸው የሰልጣኞች ተሳትፎ ማሳደግ
- በሁሉም ሥልጠና ፕሮግራሞች የሱቶችና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ ማሳደግ
- በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ ያደጉ የተቋም አመራሮችና መመደብ
- የዘርፉ አመራሮችን በብቃት ማዕቀፉ መሰረት በአጫጭርና በመደበኛ ስልጠና ስልጠና ማብቃት
- ለተቋማት አመራሮች የማበረታቻ ስርዓት መዘረጋት
- ለተቋማት አመራሮችየሙያ ፈቃድ መስጠት
- ተቋማት የቦርድ አስተዳደር ስርዓትን እንዲተገብሩ ማድረግ
- ተከታታይ የሴት አመራሮች አቅም ግንባታ ፓኬጅ ማዘጋጀት
- በቴ/ሙ/ስ ተቋማት የሴት አመራሮች ተሳትፎ ምጣኔ ማሳደግ
- በስልጠና ተቋማት ደረጃ በዲንና ም/ል ዲን ሴት አመራሮችን መመደብ
አገልግሎት ፈላጊዉ መሟላት ያለበት ጥያቄዎች /ቅድመ-ሁኔታዎች/
- የሥራ ገበያ ፍላጎት የጥናት ሰኔድ ይሰጠኝ ጥያቄ
- የሥራ ገበያ ፍላጎት ተንተርሶ የሰዉ ኃይል ይሟላልኝ ጥያቄ
- የአቅም ግምባታ ጥያቄ
- የመንግስት፣የግልና መያድ ማሰልጠኛ ተቋማት የድጋፍና ክትትል ፍላጎት
- የሥልጠና ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ፍላጎት/Authentication ጥያቄ
- የሥልጠና መሣሪያዎችና ሌሎች መመርያዎች ፍላጎት ጥያቄ
- የዘመኑን አገር አቀፍና ክልል አቀፍ የመመዝገቢያና የመግቢያ መሰፍርት ይሰጠኝ ጥያቄ
- በጋራ ለመሥራት የጋራ ሰኔድ(memorandum)የመፈራረም ጥያቄ
- ኮሌጆች የማወዳደርያ መሰፍርት ጥያቄ
- የሙያ ማሻሻያ፤የመመልመያና ሌሎች የማመሳከርያ ሰኔዶች ይሰጠኝ ጥያቄ
- ሥልጠና ለመሥጠት የሚያገለግሉ የተለያዩ የስልጠና ማቴርያሎች( soft and hard copy )ጥያቄ
- ብቁና ተወዳዳሪ ኢንተርፕራይዞች እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ የመንግስት ፖሊሲ/
- ስትራቴጂና የተገልጋዮች ፍላጎት/ጥያቄ
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች የፕሮግራምምዝገባ፣ እውቅና፣ የደረጃ ማሳደግ፣ የፕሮግራም ማስፋፋትና እድሳት እውቅና ጥያቄ
- የሥልጠና መሣሪያዎች አቅርቦት ፍላጎት
- የሥራ ገበያ ፍለጎት ፍላጎት ተተንርሶ ሰዉ ኃይል ይሟላልኝ ጥያቄ
- የአቅም ግንባታ ፍላጎት /ጥያቄ ፣