ሰላማዊ የኢንዳስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡዋና ዋና አገልግሎቶች
1.የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የህግ ማዕቀፎችና የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣
- የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የህግ ማዕቀፎች፣ፖሊሲዎች፣ደንቦች፣መመሪያዎችና ኮንቬንሽኖች በተመለከተ በአሰሪዎች፣ሠራተኞችና የሚመለከታቸው አካላት ዘንድ ንቃተ ህግ እንዲፈጠር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠናዎችንና የአድቮከሲ ሥራዎችን ማካሄድ፣
- የሥራ አካባቢዎችና የሥራ ሁኔታዎችን ለማሻሻል የሚረዱ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና ሥራ አካባቢ ጥበቃንና የመሠረታዊ ሥራ ሁኔታዎች አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ጥምር የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥሮችን ማካሄድ፣
- በመከላከል፣ከለላ በመስጠትና በመልሶ ማቋቋም መርህ ላይ በመመስረት በድርጅቶች ውስጥ አስከፊ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን መቆጣጠር፣ መከታተል፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
- በድርጅቶች የሙያ ደህንነትና ጤንነት አመራር ሥርዓትን መዘርጋትና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
- በሙያ ደህንነትና ጤንነት ዘርፍ በማመከር አገልገሎት ለሚሠማሩ የግል ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት፣
- የሥራ ቦታ ትብብርና የማህበራዊ ምክክር ስርዓትን በድርጅት ደረጃ መዘርጋትና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
- በአሠሪና በሰራተኞች መካከል የሚከሰቱ የሥራ ክርክሮችን በማስማማት እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በዳኝነት አገልግሎት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ፣
- አሠሪዎችና ሠራተኞች ጥቅሞቻቸውንና መብቶቻቸውን ለማስከበር በህግ የተሰጣቸው በማህበር የመደራጀትና የህብረት ድርድር የማድረግ መብቶቻቸው መከበራቸውን ለማረጋገጥ መከታተልና ድጋፍ ማድረግ፣
- የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራትንና የህብረት ሥምምነትን መመርመር፣ መመዝገብና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፣
- የሥራ ሁኔታዎች መቆጣጠሪያ አገልግሎትን የማስፈጸም አቅምና የቴክኒካዊ የብቃት ደረጃ ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዱ የማቴሪያልና የባለሙዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማካሄድ፣
- አዳዲስ ድርጅቶች ሲቋቋሙ፣ ሲስፋፉ፣ ስራቸውን ሲቀይሩ የሥራ ሁኔታቸው በሰራተኞች ደህንነትና ጤንነት ላይ ጉዳት የማያስከትሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ የብቃት ማረጋገጫ መስጠት
- ማህበር ባልተደራጀባቸው ድርጅቶች ሠራተኞች በማህበር የመደራጀት መብቶቻቸውን እንዲጠቀሙ ለማበረታታትና ለመደገፍ የሚያስችል ሥርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ
- ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ ቁጥጥር ማድረግ
ከተገልጋዮች የሚጠበቁ ጉዳዮች
- የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት በሕግ መሠረት የመደራጀት መብታቸውን ተጠቅመው ማህበር ከመሰረቱ በኃላ ህጋዊ ሰውነት ለማግኘት የማህበሩን መረጃ ማቅረብ
- አዲስ የህብረት ስምምነትን ለማስመዝገብ፣ለማደስና ለማሻሻል ስፈልጉ አሰሪዎችና የሰራተኛ ማህበር አባላት የተፈራረሙበትን ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በህግ ውስጥ የተቀመጡ መብትና ግዴታ ከተወጡ ከ60 ቀን በኋላ ከእኛ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ
- በማህበር አመራር አባላት በኩል የወል የስራ ክርክር ለቋሚ ወሳኝ ቦረድ ማቅረብ፣
- የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 የአሠሪና ሠራተኛን መሠረታዊ መብቶችን በመጠቀም የወል የስራ ክርክር ማቅረብ
- ማንኛዉም በ1156/2011 አዋጅ መሠረት በሚተዳደሩ ድርጅቶች ዉስጥ ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሠራተኞች በስራ ቦታ በደል ደረሰብን የሚሉ ተበዳዮች ቅሬታቸዉን በጽሑፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል