Employer and employee development sector
1. ሰላማዊ የኢንዳስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትየሚሰጡ ዋናዋና አገልግሎቶች
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የህግ ማዕቀፎችና የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ የህግ ማዕቀፎች፣ፖሊሲዎች፣ደንቦች፣መመሪያዎችና ኮንቬንሽኖች በተመለከተ በአሰሪዎች፣ሠራተኞችና የሚመለከታቸው አካላት ዘንድ ንቃተ ህግ እንዲፈጠር የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠናዎችንና የአድቮከሲ ሥራዎችን ማካሄድ፣
የሥራ አካባቢዎችና የሥራ ሁኔታዎችን ለማሻሻል የሚረዱ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነትና ሥራ አካባቢ ጥበቃንና የመሠረታዊ ሥራ ሁኔታዎች አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ጥምር የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥሮችን ማካሄድ፣
በመከላከል፣ከለላ በመስጠትና በመልሶ ማቋቋም መርህ ላይ በመመስረት በድርጅቶች ውስጥ አስከፊ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን መቆጣጠር፣ መከታተል፣ የምክርና የቴክኒክ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
በድርጅቶች የሙያ ደህንነትና ጤንነት አመራር ሥርዓትን መዘርጋትና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
በሙያ ደህንነትና ጤንነት ዘርፍ በማመከር አገልገሎት ለሚሠማሩ የግል ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠት፣
የሥራ ቦታ ትብብርና የማህበራዊ ምክክር ስርዓትን በድርጅት ደረጃ መዘርጋትና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
በአሠሪና በሰራተኞች መካከል የሚከሰቱ የሥራ ክርክሮችን በማስማማት እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በዳኝነት አገልግሎት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ፣
አሠሪዎችና ሠራተኞች ጥቅሞቻቸውንና መብቶቻቸውን ለማስከበር በህግ የተሰጣቸው በማህበር የመደራጀትና የህብረት ድርድር የማድረግ መብቶቻቸው መከበራቸውን ለማረጋገጥ መከታተልና ድጋፍ ማድረግ፣
የአሠሪና ሠራተኛ ማህበራትንና የህብረት ሥምምነትን መመርመር፣ መመዝገብና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፣
የሥራ ሁኔታዎች መቆጣጠሪያ አገልግሎትን የማስፈጸም አቅምና የቴክኒካዊ የብቃት ደረጃ ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዱ የማቴሪያልና የባለሙዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማካሄድ፣
2. የሥራ ሥምሪት አገልግሎት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
የተቋሙ ፖሊስዎች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች፤ ኮንቬንሽኖች፤ መርሀ-ግብሮች ዙሪያ የግንዛቤ ማዳበሪያ ስልጠና፤ የአድቮኬሲ አገልግሎት መስጠት፤
የሰው ኃይል አቅርቦትና ፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት መሰረት ያደረገ የተሟላና ወቅታዊ የሥራ ገበያ መረጃዎችንተደራሽ ማድረግ፣
ዜጎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸዉ በፊትና በስራ ላይ እያሉ ከስራ ባህልና አጠቃላይ ከስራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
በክልል ዉስጥና ከክልል ዉጪ በሚገኙ የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀይል ጥያቄ ተቀብሎ ሥራና ሠራተኛን የማገናኘት ነፃ የሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት፣
ሥራ አጦችንና ሥራ ፈላጊዎችን፣ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የመመዝገብ አገልግሎት፣
ለአገር ዉስጥ እና ለዉጭ አገር የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የቅድመ ፈቃድ/የቅርንጫፍ ፈቃድ/እድሳት ቁጥጥር፣ ክትትል ድጋፍ አገልግሎት፣
ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ዜጎች በቴክኒክ ሙያ የክህሎት ሥልጠና የድጋፍና ክትትል እና የቅድመ-ጉዞ ትምህርትና ስልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
ለሥራ አጦችና ሥራ ፈላጊዎች የቅድመ-ሥራ ሥምሪት ሥልጠና የመስጠት አገልግሎት፣
የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን መከላከል፣
የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አገልግሎት መስጠት